Menu
  • HOME
  • ENGLISH
    • Prayer
    • Verses
    • Songs
    • Movie
    • Gallery
    • About
    • About US
  • አማርኛ
    • ጸሎት
    • ቃል
    • መዝሙር
    • ፊልም
    • የፎቶ ማዕከለ
    • ስለ
    • ስለ እኛ
 ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ 'ዘኁልቍ 6:24

'The Lord bless thee, and keep thee: 'Numbers 6:24

Showing posts with label ጸሎት. Show all posts
Showing posts with label ጸሎት. Show all posts

የአዲስ ዓመት ጸሎት

By  WISDOMጸሎት No comments:

መንፈስ ቅዱስ   ዛሬ እና ሁል ጊዜም ከእኛ ጋር ይሁኑ ፡፡
ብርሃናችን ፣ መመሪያችን እና አፅናኛቺን ይሁን ።
ብርታታችን ፣ ድፍረታችን እና ቅድስናችን ይሁን ።
ይህ አዲስ ዓመት ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ እድገት ዓመት ይሁን ፣
መንፈሳዊ ፀጋዎች  እና ስጦታዎችዎን የምንቀበልበት ዘመን ይሁን ፣
በሙሉ ልብ ይቅር የምንባባልበት ዘመን ይሁን ፣
በመልካም ማደግና የመፅናት  ዘመን ይሆን ዘንድ
መንፈስ ቅዱስ ከሁላችንም ጋር  ፣
ዛሬ እና ሁል ጊዜም ከእኛ ጋር ይሁን ፡፡

Read More

ክርስቶስን ለመቀበል

By  WISDOMጸሎት No comments:
ሕይወት>
1.ችግርህን እወቅ (ኃጢአተኛ መሆንህን)
2.ከኃጢአትህ ለመመለስ ፍቃዳኛ ሁን (ንስሃ ግባ)
3.ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ኃጢአት እንደ ሞተና እንደ ተነሣ እመን
4.ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ ሕይወትህ እንዲመጣና ሕይወትህን እንዲቆጣጠር በጸሎት ጋብዘው፥ (እርሱ ብቻ አዳኝህ እንደሆነ ተቀበል )
ይህን ጸሎት
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ
እንደሆንኩ አውቃለሁ፥አንተም የኃጢአቴን
ቅጣት ለመክፈል እንደ ሞትክ አምናለሁ ::
ኃጢአቴንም ትቼ አንተን ለመከተል እፈልጋለሁ ፥
ወደ ሕይወቴና ልቤ እንድትመጣ እጋብዛለሁ ::
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፤
አሜን !
Read More

ለአዲስ ዓመት ጸሎት

By  WISDOMጸሎት No comments:
ለአዲስ ዓመት ጸሎት
አባት ሆይ የዘመኑ መቀየር ከቁጥር በዘለለ የእኛውም አስተሳሰብ እንዲቀየር ነው፡፡ ለሥጋዊ ኑሮአችን መሳካት በእቅድ እንደምንመራው ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን እንድናስብ፤ ቃለ እግዚአብሔር ለመማር፣ ንስሐ ለመግባት፣የመድሐኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል መንፈሳዊ እቅድ እድናወጣ ተግባራዊ ለማድረግም ጥረት እንድናደርግ እንድትረዳን እንጸልያለን። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፣ሕይወትዎን ያድስ፣የመጽናናት፣ የፍቅር እንዲሁም ዘምኑ የበረከት ዘመን ለእናተ እና ለእናተ ለሆኑት ሁሉ ይሁን በኢየሱስ ስም አሜን!
መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችሁም!

Read More

ገናን በማስመልከት ጸሎት

By  WISDOMጸሎት No comments:

ገናን በማስመልከት ጸሎት
ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይገባሃል በዚህች የመታሰቢያ ቀን የመድሐኒታችን ውድ ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በባህላዊና ተለምዶዋዊ አከባበር ብቻ እንዳናሳልፍ ይህ ታላቅ ቀን ለዘላለማዊ ጥሪ የህዝብሕን ሐጢያት ሊቀበልና በእርሱ የዘላለሙን ህይወትን እንድናገኝ የመጣውን እንደቃልህ ከሴት የተወለደውን በማሰብ በእምነት በመቀበል ከልዑላዊ ህይወት፣ሰላምና ፍቅርህ እንዳንታጣ ትረዳን ዘንድ ሕዝብህንም ትጠራ ዘንድ በጌታ ኢየሱስ ስም ጸለይኩ ።

Read More

ይጸልይ ነበር

By  WISDOMጸሎት No comments:
ኢየሱስ … ይጸልይ ነበር
 1/ በኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ ጸሎት ምን ያህል ወሳኝ ስፍራ እንደነበረው ሉቃስ  ይገልፃል በዮርዳኖስ መንፈስቅዱስ  በኢየሱስ ላይ በወረደ ጊዜ እርሱ እየጸለየ ነበር። ሉቃ 3:21  ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥ሉቃ 5:16 ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር። ሉቃ 6:12  በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ። ሉቃ 9:18 ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና። ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ሉቃ 9:28 ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሉቃ 9:29 ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ። ሉቃ 11:1 እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ። ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው ሉቃ 22:42 ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃ 23:34  ኢየሱስም። አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።ሉቃ 23:46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
 2/ በሌሎች ወንጌሎች ውስጥ የኢየሱስ ሕይወት ምን እንደሚመስል በምንመረመርበት ጊዜ ኢየሱስ “እናንተ ሽክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ ፤”ብሎ ለስዎች ጥሪ ከማደረጉ በፊት እንደጸለየ እናያለን ኢየሱስ በዓላዛር መቃብር ላይ “ዮሐ 11፡41 ድንጋዩንም አነሡት። ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። አባትሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻው ጊዜ ያደርግ ነበር እያንድንዱ አማኝ መንፈሳዊ ሕይወቱ በመልካም ሁኔታ ይገኝ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻው ጊዜ እንዲኖረው ያስፈልገዋል። የግል የጸሎት ጊዜ ፍላጎት አለመኖርና ከሰማያዊ አባታችን ጋር ኅብረት አለመሻት በውስጣችን ያለው መንፈሳዊ ሕይወት ለመውደቅ በማሽቆልቆል ሂደት ላይ እንዳል የሚይሳይ የማያጠራጥር ምልክት ነው። ይህ እየሆነ ካለ እግዚአብሔርን ከሚያሳዝነው ነገር ሁሉ በመመለስ፤እግዚአብሔርንና የማዳን ጸጋውን ለመሻት ያለንን ጽኑ ውሳኔ ማደስ ይኖርብናል።
Read More

ሰላምን እተውላችኋለሁ

By  WISDOMጸሎት No comments:

ሰላምን እተውላችኋለሁ
ስላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም።ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። ዮሐ 14:27               
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ለሐዋርያት እንዲህ እንዳልካቸው; እኔ ለእናተ ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤እንዳልክ ኃጢአታችንን ይቅር በል ቤተክርስቲያንህንም በእምነት, እና በአንተ ፈቃድ በመስማማት በመንገድህ በእውነትህ   ሰላምና አንድነት በመስጠት አጽናት ሁሉንም የምታይና የምትግዛ አምላክ, መጨረሻ የሌለህ ክብር ምስጋና ይገባሃል ተባርክ ተመስገን ።
                                 በመዳሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!
Read More

ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር

By  WISDOMጸሎት No comments:

Read More
Older Posts Home

Popular Posts

  • ወንጌል ምንድነው?
  • እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ
  • ፍቅር ፣ እምነት ፣ ተስፋ እና እውነት!
  • የጠፋው በግ
  • አዲስ ፍጥረት
  • ኢየሱስ ጌታ ነው
  • ኃጢአት እንዴት ወደ አለም ገባ ?
  • የእግዚአብሔር ጥበቃ
  • የእግዚአብሔር መንግሥት
  • መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት

Total Pageviews

Flag Counter

Copyright © 2016 STRENGTH IN WISDOM