እግዚአብሔር ይወድሃል፤ በሰላም እንድትኖርና የዘላለምም ሕይወት እንድታጋኝ ይወዳል::
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል…..
እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ ሮሜ 5:1
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።ዮሐ 3:16
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6:23
እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስላምና የዘላለም ሕይወት ዐቅዶልን እያለ
ለምንድን ነው ብዙ ስዎች ይህን የማይለማመዱት?
ደረጃ ፪ የስው ችግሩ:
ኃጢአትና ከእግዚአብሔር መኰብለል ነው እግዚአብሔር በግድ እርሱን እንድንወደውና እንድንታዘዘው ፍቃድና የምርጫ ነጻነትን ሰጥቶናል:: የሚያሳዝነው ልክ እንደ አዳም ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አለመታዘዝና በገዛ መንገዳችን መሄድን እንመርጣለን (ዘፍ 2:3) ይህ ባህሪያችን ኃጢአት ይባላል፤ይህም ከእግዚአብሔር ይለየናል ::
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል…..
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ …. የኃጢአት ደመወዝ ሞት…. ሮሜ 3:23 ፤ 6:23 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው:: ዘፍ 3:23
“ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል ::”
ደረጃ ፫
የእግዚአብሔር መፍትሔ መስቀሉ
ከእግዚአብሔር ጋር ያለያየንን የኃጢአት ዕዳ ይከፍልልን ዘንድ ክርስቶስ በመስቀል ላይ
ሞተ፥ ስለ እኛም ከሞት ተነሣ :: ኢየሱስ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ገደል
መሸጋገሪያ ድልድይ ሆነን :: በዚህም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ላለው ችግር ብቸኛ
መፍትሔ ሆነ ::
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል…..
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5:8
“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” ሐዋ 4:12
“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ “ 1ኛ ጢሞ 2:5
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” ዮሐ 5:24
እግዚአብሔር ብቸኛ መንገድ ሰጥቶአል :: ይህን መምረጥ የእኛ ፈንታ ነው ::
ደረጃ ፬
ከእኛ የሚፈለግ ምላሽ ክርስቶስን መቀበል
በክርስቶስ መልዕክት እና በእርሱም ብቸኛ አዳኝነት በማመን ክርስቶስን መቀበል እንችላለን ::
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል…..
በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል። ሐዋ 10:43
ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐ 14:1
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሐ 1:12፤
ክርስቶስን ለመቀበል
1. ችግርህን እወቅ (ኃጢአተኛ መሆንህን)
2.ከኃጢአትህ ለመመለስ ፍቃዳኛ ሁን (ንስሃ ግባ)
3. ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ኃጢአት እንደ ሞተና እንደ ተነሣ እመን
4. ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ ሕይወትህ እንዲመጣና ሕይወትህን እንዲቆጣጠር በጸሎት ጋብዘው፥ (እርሱ ብቻ አዳኝህ እንደሆነ ተቀበል )
ይህን ጸሎት
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ
እንደሆንኩ አውቃለሁ፥አንተም የኃጢአቴን
ቅጣት ለመክፈል እንደ ሞትክ አምናለሁ ::
ኃጢአቴንም ትቼ አንተን ለመከተል እፈልጋለሁ ፥
ወደ ሕይወቴና ልቤ እንድትመጣ እጋብዛለሁ ::
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፤
አሜን !
የጌታ ዋስትና በቃሉ በእርግጥ ይህንን ከልብህ ጸልየህ ከሆነና ኢየሱስ ክርስቶስ ወደሕይወትህ
እንዲመጣ ከለመንህ ፤እግዚአብሔር ምንድን እንደ ስጠህ ታውቃለህን?
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል…..
የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። “ሮሜ 10:13 ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።” ሮሜ 8:39 እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን። “ሮሜ 5:1 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ፣ የዘላለም
ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፤1ኛ ዮሐ. 5:12-13
አዲሱ ሕይወትህ ፤
ክርስቶስን ስትቀበል በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አሠራር የእግዚአብሔር ቤተስብ ሆነሃል፡፡ወደዚህ የእግዚአብሔር ቤተስብ የረዳህ መንፈስቅዱስ፤ በአንተ ውስጥ ማደሪያውን አድርጓል ፡፡ይህ ድንቅ ሕይወት ዳግም ከእግዚአብሔርመወለድ ይባላል፡፡በጀመርከው በዚህ ድንቅ የሆነ አዲስ ሕይወት እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡
በዶ/ር ቢሊ ግራሃም
No comments:
Post a Comment