Menu
  • HOME
  • ENGLISH
    • Prayer
    • Verses
    • Songs
    • Movie
    • Gallery
    • About
    • About US
  • አማርኛ
    • ጸሎት
    • ቃል
    • መዝሙር
    • ፊልም
    • የፎቶ ማዕከለ
    • ስለ
    • ስለ እኛ
 ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ 'ዘኁልቍ 6:24

'The Lord bless thee, and keep thee: 'Numbers 6:24

የጠፋው በግ

By  WISDOM No comments:
የጠፋው በግ
መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ። የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።ሉቃስ 15:4-7 
በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ዋና የሆነው ጥቅስ “የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው”  የሚለው ነው ከዚህም የምንማረው፤
1)ይድኑ ዘንድ በኅጢአት የጠፉትን መፈለግ፤በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ አስፈላጊ ነገር እንደ ሆነ፤
2)አንድ ኅጢአተኛ እንኳ ንስሓ ቢገባ በእግዚአብሔር ዘንድና በስማይ ታላቅ ደስታ እንደሚሆን፤
3)የጠፋውን ፈልጎ ወደ ኢየሱስ ለማምጣት ማንኛውንም መሥዋዕትነት ቢከፈልና ማንኛውንም መከራ ቢገባም ብዙ እንዳልሆነ፤
4)በሰማይም እግዚአብሔርና መላእክቱ በኅጢአት ለወደቁትና በመንፈሳዊ ሞት ውስጥ ለሚገኙት እንደዚህ ዐይነት ርኅራሔና አዜነታ ስላላቸው አንድ ኅጢአተኛ ንስሓ በሚገባበት ጊዜ በግልጽ ሐሤት ያደርጋሉ፡፡
እግዚአብሔር ለኅጢአተኛ ያለውን ፍቅር ለመረዳት፤
ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው ።
'በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። 'ፊልጵስዩስ 2:5-8
Newer Post Older Post Home

No comments:

Post a Comment

Popular Posts

  • ወንጌል ምንድነው?
  • የእግዚአብሔር መንግሥት
  • የሕይወት መንገድ
  • የእግዚአብሔር ጥበቃ
  • መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት
  • ብርታት ከእግዚአብሔር ጥበብ
  • ታዛዥነት
  • ኢየሱስ ጌታ ነው
  • ኃጢአት እንዴት ወደ አለም ገባ ?
  • ፍቅር ፣ እምነት ፣ ተስፋ እና እውነት!

Total Pageviews

Flag Counter

Copyright © 2016 STRENGTH IN WISDOM