ወደ ሮሜ ሰዎች። 5:17
ሞት በአዳም፣ ሕይወት በክርስቶስ
በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። ኃጢአት በአንድ ስው በኩል ወደ አለም ገባ፡፡ (ኦሪት ዘፍ 3:17-19) 17፤ አዳምንም አለው ። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፡፡ 18፤
እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።19፤ ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።(1 ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ . 15:21-22) 21 ፤ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና ።
22 ፤ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና በአዳም ውድቀት ምክንያት ኃጢአት ወደ ሰው ዘር ገባ ፡፡ከዚህም የተነሣ እነዚህ ውጤቶች ተከሰቱ፡፡
1)በአዳም ምክንያት ኃጢአት ወደ ሰው ዘር ሁሉ ተላለፈ፡፡ ኦሪት ዘፍ 6:5-12) 5፤
እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። 6፤
እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ። 7፤
እግዚአብሔርም። የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና አለ። 8፤ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ። 9፤ የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ። 10፤
ኖኅም ሦስት ልጆችን ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ። 11፤ ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸች፤ ምድርም ግፍን ተሞላች። 12፤
እግዚአብሔርም ምድርን አየ፥ እነሆም ተበላሸች፤ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና። 1ዮሐ 5:19 ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
2) ሞት በኅጢአት ምክንያት ወደ ዓለም የገባ ሲሆን ሁሉም ኅጢአትን ሠርተዋል ስለሚል ሰው ሁሉ ይሞታል ኦሪት ዘፍ 2፡17 ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና ።ኦሪት ዘፍ 3፡23 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ የሰው ዘር የሚሞተው እንደ አዳም ፍርድ የሚያስከትለውን የእግዚአብሔርን የቃል ሕግ ስለተላለፍ በተፈጥሮውና በሥራው ኅጢአተኛ በመሆኑ እንዲሁም በልቡ የተጻፈውን የሕሊና ሕግ ተላላፍ ስለሆነ ነው፡፡ጳውሎስ የውድቀትን መዘዝ ሊሽር የሚችለውን በኢየሱስ ክርስቶስ የቀረበውን መዋጀት ፍጹም ብቃት እንዳለው ይገልጻል ፡፡ ይህ የመልክቱ ዋና ሐሳብ ነው፡ አዳም ኅጢአትንና ሞትን አስከተለ ክርስቶስ ደግሞ ጸጋንና ሕይወትን አመጣ፡፡(ሮሜ 5;14-15 ) 14 ፤ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። 15፤
ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።
Constitution of Federal Democratic Republic of Ethiopia proclamation no.1/1995 Which enter in to force on 21August 1995. Article 6 and 7 govern the right to Nationality including Article 13 of the 1948 Universal Declaration of Human Right............ Federal Democratic Republic of Ethiopia.......... Article 95.Revenu which proclamation no.175/2012
ReplyDelete