1/ በኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ ጸሎት ምን ያህል ወሳኝ ስፍራ እንደነበረው ሉቃስ ይገልፃል በዮርዳኖስ መንፈስቅዱስ በኢየሱስ ላይ በወረደ ጊዜ እርሱ እየጸለየ ነበር። ሉቃ 3:21 ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥ሉቃ
5:16 ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር። ሉቃ 6:12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ
እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ። ሉቃ 9:18 ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና። ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ሉቃ 9:28 ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሉቃ 9:29 ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ። ሉቃ 11:1 እርሱም በአንድ ስፍራ
ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ። ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን
አለው ሉቃ 22:42 ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃ 23:34 ኢየሱስም። አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።ሉቃ 23:46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
2/ በሌሎች ወንጌሎች
ውስጥ የኢየሱስ ሕይወት ምን እንደሚመስል በምንመረመርበት ጊዜ ኢየሱስ “እናንተ ሽክም የከበዳችሁና የደከማችሁ
ሁሉ ወደ እኔ ኑ ፤”ብሎ ለስዎች ጥሪ ከማደረጉ በፊት እንደጸለየ እናያለን ኢየሱስ በዓላዛር መቃብር ላይ “ዮሐ 11፡41 ድንጋዩንም
አነሡት። ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። አባትሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር
ጋር ለብቻው ጊዜ ያደርግ ነበር እያንድንዱ አማኝ መንፈሳዊ ሕይወቱ በመልካም ሁኔታ ይገኝ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻው ጊዜ
እንዲኖረው ያስፈልገዋል። የግል የጸሎት ጊዜ ፍላጎት አለመኖርና ከሰማያዊ አባታችን ጋር ኅብረት አለመሻት በውስጣችን ያለው መንፈሳዊ
ሕይወት ለመውደቅ በማሽቆልቆል ሂደት ላይ እንዳል የሚይሳይ የማያጠራጥር ምልክት ነው። ይህ እየሆነ ካለ እግዚአብሔርን ከሚያሳዝነው
ነገር ሁሉ በመመለስ፤እግዚአብሔርንና የማዳን ጸጋውን ለመሻት ያለንን ጽኑ ውሳኔ ማደስ ይኖርብናል።
No comments:
Post a Comment