Menu
  • HOME
  • ENGLISH
    • Prayer
    • Verses
    • Songs
    • Movie
    • Gallery
    • About
    • About US
  • አማርኛ
    • ጸሎት
    • ቃል
    • መዝሙር
    • ፊልም
    • የፎቶ ማዕከለ
    • ስለ
    • ስለ እኛ
 ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ 'ዘኁልቍ 6:24

'The Lord bless thee, and keep thee: 'Numbers 6:24

መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት

By  WISDOM 2 comments:
1. የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንረዳለን:: መዝ  119:105  ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
2. መንፈሳዊ ጉድለታችንን አውቀን ለማስተካከል እንችላለን! ያዕ 1:22-23 ፤ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ፤ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
3. የተሻለ ሕይወት እንድንኖር ይረዳናል :: ማቴ 4:4 ፤ እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው  ኤር 29:11 ፤ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
4. እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማወቅ ይረዳናል::  ሮሜ 10:17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።1 ጴጥ 2:2-3  ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።
5. የሕይወት መንገዳችንን ይመራናል::  (ኢያሱ 1:8) የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።
6. መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ  እግዚአብሔር እንዳንበድል ይረዳናል ። . መዝ 119:11   አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
7. ከህይወታችን የማያስፈልገውን ይቆርጣል እኛንም ያሳድገናል :: ኤፈ 6:17 ፣ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
8. ፍሬያማዎች ያደርገናል :: ቆላ 1:11 በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
9. መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እኛ ስለ ወንጌል እንማራለን ፤ ዮሐ 5:39-40 ፤ እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤  ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።
10. በእምነት ለማደግ መጽሐፍ ቅዱስን  ማጥናት ይጠቅማል:: ሮሜ 10:17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
11. በጥበብ ለማደግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይረዳናል:: መዝ 119:98 ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
12. መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ከሁሉ በላይ  ኢየሱስን ለማወቅ ይረዳናል ።ማቴ 5:17እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።  ሉቃ 24:44 እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።ዮሐ 5:39እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
13. ከሐሰት ትምህርቶችና ሐሰተኛ ነቢያት ራስህን ለመጠበቅ ይረዳናል :: ማቴ 7:15የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ቆላ 2:8 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ  ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ። 
14. ጊዜያችንን በጥበብ   ለመጠቀም:: ኤፌ 5:15-16 እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ  በጥንቃቄ ተጠበቁ፤  ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።

Newer Post Older Post Home

2 comments:

  1. AnonymousOctober 26, 2022 at 5:06 PM

    Abagolerblan28@yahoo.com

    ReplyDelete
    Replies
      Reply
  2. AnonymousMarch 15, 2025 at 7:39 AM

    Really it is good expression and I got alot from this matrial God bless you

    ReplyDelete
    Replies
      Reply
Add comment
Load more...

Popular Posts

  • የእግዚአብሔር መንግሥት
  • ወንጌል ምንድነው?
  • የሕይወት መንገድ
  • የእግዚአብሔር ጥበቃ
  • ብርታት ከእግዚአብሔር ጥበብ
  • መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት
  • ኢየሱስ ጌታ ነው
  • ታዛዥነት
  • ኃጢአት እንዴት ወደ አለም ገባ ?
  • Standing Firm | Full Movie | God’s Sovereignty In Our Struggles

Total Pageviews

Flag Counter

Copyright © 2016 STRENGTH IN WISDOM