ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ መልካም የምሥራች ነው፡፡ የንስሐ፣ የመፍትሄ፣ የሰላም፣ የደኅንነት፣ የእርቅ፣ ከፍርድ የመዳን አዋጅ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መንግስት አዋጅ የሆነውን ወንጌል አስቀድሞ እንደሰበከ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ('ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም
ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር። 'ማቴዎስ 4:23፣ 'ዮሐንስ እስር ቤት ከገባ
በኋላ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ ሄዶ፣ “ጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ
ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ይሰብክ ነበር። 'ማርቆስ 1:14-15) ፡፡ የወንጌል አንኳር መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። ሰዎች ከእግዚአብሄር ቁጣ እንዲተርፉ፤ኃጢአት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ክርስቶስ እየሱስ የሰው ልጆች ምትክ ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን ማወጅ ነው ('ለሞት የሚያበቃው አንድም ምክንያት ባያገኙበትም እንኳ ጲላጦስ የሞት ፍርድ
እንዲፈርድበት ተማጸኑት። ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ ከፈጸሙ በኋላ ከተሰቀለበት ዕንጨት አውርደው በመቃብር ውስጥ አስገቡት። እግዚአብሔር
ግን ከሙታን አስነሣው። 'ሐዋርያት ሥራ 13:28-30፣'። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤ 'ሐዋርያት ሥራ 13:38። 'በደሙም በሆነው እምነት፣
እግዚአብሔር የማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ
ጽድቁን ለማሳየት ነው፤ በአሁኑ ዘመን ይህን ያደረገው፣ ጽድቁን ይኸውም እርሱ ራሱ ጻድቅ ሆኖ፣ በኢየሱስ የሚያምነውን የሚያጸድቅ
መሆኑን፣ ለማሳየት ነው። 'ሮሜ 3:25-26፣ 'እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ '1 ቆሮንቶስ 15:3-4) ።
ወንጌል የምሥራች ነው ሲባል፣ በመስቀል ላይ ክርስቶስ ኢየሱስ በፈጸመው የድኅነት ሥራ ለሚያምነው ሰው ያስገኘው ትሩፋት ምትክ የለሽ መሆኑን በማሣየት ነው፡፡
የሰው ልጅ በመስቀል ላይ በተሰራው የድኅነት ሥራ በማመን የኃጢአት ሥርየትን ያገኛል
የሰው ልጅ በመስቀል ላይ በተሰራው የድኅነት ሥራ በማመን የኃጢአት ሥርየትን ያገኛል
- ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እርቅን ያገኛል
- የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን መብት ይጎናፀፋል
- የእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግስት ዜግነትን ያገኛል
- ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ቀደመው የፍቅር ህብረት ይመለሳል
- በዚህ ዓለም ሲኖር የዘላለማዊ ተስፋ መታደስን ያገኛል
- ዘላለማዊ አድራሻው ከሞት ወደ ህይወት ይለወጣል
- የምሥራቹን ወንጌል የማወጅ መብትና ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል
- በኃጢአት ምንክንያት ከሚመጣ የእግዚአብሔር ፍርድ ይድናል
የወንጌል ዋና መልእክት ምንድነው?
የወንጌል አንኳር መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። የድኅነት ሥራ በክርስቶስ ተፈፅሟል የአዋጁ ዋና መልዕክት ነው (የድህነት ሥራ በክርስቶስ ተፈፅሟል የአዋጁ ዋና መልዕክት ነው።'ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም እንዲሰረይላችሁ፣ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። 'ሐዋርያት ሥራ 2:38፣'እርሱም ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአትን ስርየት ይሰጥ ዘንድ፣ እግዚአብሔር የሁሉ ራስና አዳኝ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው። 'ሐዋርያት ሥራ 5:31፣'በእርሱም የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ስርየት እንደሚቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።” 'ሐዋርያት ሥራ 10:43፣'አንተም ዐይናቸውን ትከፍታለህ፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸዋለህ፤ እነርሱም የኀጢአትን ይቅርታ ይቀበላሉ፤ በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስት ያገኛሉ።’ 'ሐዋርያት ሥራ 26:18) ። የድኅነት ስራ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለተከናወነ፣ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ እና የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ የሚነገር የምስራች ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው ወንጌል በመስቀል ላይ የተከናወነውን አስደናቂ የድኅነት ስራ የማወጅ ተግባር ነው፣ “መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ..” (1ቆሮ 5፡1-4)።
የክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ የወንጌል ማዕከል ነው። ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ የሚታወጅ የመስቀሉ የማዳን ሥራ ነው፣ “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው…” (1ኛ ጢሞ.1፡15)። ወንጌል ሰዎች ከኃጢአታቸው ንስሃ በመግባት የበደላቸውን ስርየት እንዲቀበሉ ይናገራል፣ “..በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል” (ሉቃ 24፡47) ።
ኢየሱስ ይሄን ወንጌል ሰብኳል፣ “ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ” (ማርቆ 1፡14-15)።መጽሐፍ እንደሚል “በልጁ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው” ('በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።”'ዮሐንስ 3:36)። በኃጢአት ምክንያት ከሚመጣ የዘላለምም ፍርድ ያመልጣል፣ “በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም..”(ዮሐንስ 3፡18)።
ይሄንን የድኸነት ወንጌል ሐዋርያትም ሰብከውታል፣ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ” (ሐዋ.2፡38)።የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶችም ሰብከውታል፣ የተሃድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች አውጀውታል፣እኛም እንድናውጀው ተጠብቆብናል።
Yes
ReplyDeleteጸጋውን ያብዛልን !
ReplyDeleteWOW
ReplyDelete