የእግዚአብሔር ጥበቃ
'በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ። እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል። የሌሊትን አስደንጋጭነት፣ በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤ በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣ በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም። በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ። እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና። ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና። እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣ በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል። በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ። “ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ። ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ። ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”'መዝሙር 91:1-16
በእግዚአብሔር በሙሉ እምነታቸውን
የጣሉት የቱን ያህል ዋስትና እንዳላቸው ይገልጻል።እግዚአብሔር መጠጊያችን እንደሚሆን፣ከዚህም የተነሣ መንፈሳዊና ሥጋዊ አደጋ ሲመጣ
ጥበቃውን ልንፈልግ እንድምንችል ያረጋግጥናል።
'በእግዚአብሔር የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ በወጥመዳቸው ተያዘ፤ በጥላው ሥር፣ በአሕዛብ መካከል እንኖራለን ብለን አስበን ነበር። 'ሰቆቃወ 4:20
ለእግዚአብሔር ልጆች ይኸውም
ራሳቸውን ለልዑል እግዚአብሔር ፈቃድና ጥበቃ አሳልፈው ለሰጡት፣በእግዚአብሔር ህልዎትም ዕለት ተዕለት ለመኖር ለሚፈልጉት ዋስትና
ይሰጣል።
'አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤ በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤ የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤ በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ። 'ኢሳይያስ 49:2
'ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ። 'መዝሙር 63:2
' “አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ አንቺ ኢየሩሳሌም! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን ፈቃደኛ አልሆናችሁም፤ 'ማቴዎስ 23:37
1.ከሁሉ በላይ የሆነውንና ኃይሉን አምላክ መጠጊያው አድርጎ የሚኖር ሰው የሕይወቱ ዋስትና የሚያስተማምን
በመሆኑ እግዚአብሔር መጠጊያዬና ምሽጌ የምተማመንበት ፈጣሪዬም ነው ብሎ ይመሰክራል።
2.እግዚአብሔር ሕዝቡን
ከጠላት ይጠብቃል፣በላባዎቹ ይጋርዳቸዋል፣ጋሻ እና መከታ ይሆናቸዋል።
3.የእግዚአብሔር ክብካቤ ጽኑና በቂ ነው ምክንያቱም እርሱ ለሕዝቡ
ታማኝ ነው።የእግዚአብሔር ጥበቃ በቀንና በሌሊት እንደ ሆነ ተፈጥሮኣዊ
በሆኑ ምክንያቶች ከሚመጣ ፍርሀትና ድንጋጤ ይጠብቀዋል።
4.እርሱ በምድር ላይ በሚሆኑ ነገሮች ሁሉ ላይ ሙሉ ሥልጣን ስላለው ለጥበቃው ወሰን የለውም።እንክብካቤውና ጥበቃው የእግዚአብሔር
ታላቅ እንደሆን ለማሳየት ሺህ እና ዐሥር ሺህ በማለት ይገልፀዋል።
5.ጻድቃን የእግዚአብሔርን ማዳን በእምነት ዐይን ማየታቸው ይበለጥ እንዲበረቱ
ያደርጋቸዋል እግዚአብሔር ጻድቃንን ለምጠበቅና ለመባረክ ቃል ገብቷል ጻድቃን የእግዚአብሔርን ፍትሕና ታማኝነት እንዲሁም የክፉዎችን
መቀጣት በዐይናቸው ይመለከታል።
6.ልዑሉንም መጠጊያቸው በማድረግ የጥበብን መንገድ እንዲከተሉ ያበረታታል እርሱ መጠጊያቸው ነው በምድር ላይ የሚሆነው
ማንኛውም ነገር በእርሱ ቁጥጥር ሥር ነው ክፉ ነገር ወይም መቅሠፍት ቢሆን ያል እርሱ ፈቃድ አይሆንም።
7.እግዚአብሔር ጻድቃን በሚሄዱበት ሁሉ ይጠብቋቸው ዘንድ መላእክቱን ያዛቸዋል።መላእክቱ ጻድቃንን ከአደጋ እንዲጠብቋቸውና እንዲታደጓቸው ታዘዋል።እግዚአብሔር
በልጆቹ ላይ ብዙ ነገር እንዲደርስ ሊፈቅድ ይችላል ይሁንና አንድም ኅይል ከእግዚአብሔር ቁጥጥር ውጭ ዕንዳልሆነ ያውቃሉ።
8.እግዚአብሔር እርሱን ለሚወዱት
እና ስሙም ለሚያውቁ ሁሉ የማዳኑን ንግር ያበሥራቸዋል።መውደድ የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ከልብ መናፈቅንና መሻትን ይሆንናቸዋል።
9.ከእርሱ ጋር ያላቸው አንድነት የሚገልጠው ኅብረታቸው በመሥመሩ ጸሎታቸው በመመለሱና በማስተዋል
ለኖሩት ሕይወት ደስ እንደሚሰኙ ያረጋግጣል ማዳኑንም ያያሉ።
10. የእግዚአብሔር ሀሳብ፤ስላምና ዘላለማዊ ሕይወት ነው ።
Constitution of Federal Democratic Republic of Ethiopia proclamation no.1/1995 Which enter in to force on August 21 1995. Article 6 and 7 govern the right to nationality including Article 13 of the 1948 Universal Declaration of Human right.
ReplyDeletegood tanks
ReplyDelete