'ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል። '
ኢሳይያስ 11:1
'ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል። '
መዝሙር 72:11
'መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፤ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ የሚወለደው
ቅዱሱ ሕፃን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። '
ሉቃስ 1:35
'ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።” '
ማቴዎስ 1:21
'ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣
የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል። '
ኢሳይያስ 9:6
'ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው። '
ሉቃስ 2:11
'ኮከቡንም ሲያዩ ከመጠን በላይ ተደሰቱ። '
ማቴዎስ 2:10
'የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” ሲሉ ጠየቁ። '
ማቴዎስ 2:2
'“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ ለሚወዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!” '
ሉቃስ 2:14
'በዚያው አገር በሌሊት መንጋቸውን ሲጠብቁ በሜዳ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። '
ሉቃስ 2:8
'መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና። '
ሉቃስ 2:10
'በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ፤ ብዙዎችም እርሱ በመወለዱ ደስ ይላቸዋል፤ '
ሉቃስ 1:14
'ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። '
1 ዮሐንስ 5:11
'በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።'
2 ቆሮንቶስ 9:15
'ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
'
ገላትያ 4:4
'ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።” '
ሉቃስ 1:37
'ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና። '
መዝሙር 107:1
ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት የሚቀበሉ በእግዚአብሔር የመፍጠር ትዕዛዝ አማካይነት አድስ ፍጥረት ነው። { 2 ቆሮ 5:17}
ReplyDelete