'ሕዝቤ ሆይ፤ ሂድ ወደ ቤትህ ግባ፤ በርህን ከኋላህ ዝጋ፤ ቍጣው እስኪያልፍ ድረስ፣ ለጥቂት ቀን ተሸሸግ። 'ኢሳይያስ 26:20
የእግዚአብሔር ቁጣ የሚይልፈበት
ጊዜ ይመጣል ይህ ቁጣ በእስራኤል ላይ የመጣ ሲሆን በምርኮው ሸመንም ሕዝቡ በእግዚአብሔር መልካም ጊዜ ይህ የመጣባቸው ፍርድ እንደሚያከትም
ዋስትና እንዳላቸው በማሰብ ራሳቸው ፍርድ እንደሚያከትም ዋስትና እንዳላቸው በማሰብ ራሳቸውን ማብረታት ይኖርባቸዋል።በሌላ በኩል
በግብፅ ላይ የምጣው የእግዚአብሔር ቁጣ እስኪቆም ድረስ እስራኤላውያን ለጥቂት ጊዜ በቤቶቻቸው መቃን ላይ በተረጨው ደም እንደ ተጋረዱ
ሁሉ አሁን ደግሞ ምናልባትም በባቢሎን ምርኮ በዙሪያቸው ካሉት አረማውያን መከለልንና መለየትን ያመለክታል።በምርኮ የነበረችው እስራኤል
ቅዱስ ሕዝብ እንድትሆን ተጠርታለች።
ዓለም በክፋት በተሞላችበት
ሞት በነገሠበትና በወደቀው ዓለም ውስጥ የመኖርን በርካታ ውጤቶች በምንጋፈጥበት በአሁኑ ወቅት ምን ልናደርግ ይገባል?ኢሳያስ ወደ ቤታችን ገብተን እንድንጠባበቅ ይመክረናል።
እግዚአብሔር ኖኅንና ቤተሰቡን
ከጥፋቱ ውኃ ለማዳን በመርከብ ውስጥ ከዘጋበት ወይም በግብፅ የነበሩት አይሁዶች መልአከ ሞት የግብፃውያንን በኩር እየገደለ ሳለ
ቤታቸውን ዘግተው ከተቀመጡበት ሁኔታ ይሆናል።'ከሕያዋንም ፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ከውጭ ዘጋበት። 'ዘፍጥረት 7:16 ፣ ' እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ አንድ ሌላ መቅሠፍት አወርድባቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፈርዖን ይለቃችኋል፤ ሲለቃችሁም አንዳችሁን ሳያስቀር ያስወጣችኋል። 'ዘፀአት 11:1
1.የእግዚአብሔር ፍርድ ከሚያመጣቸው አደጋዎች መሸሸግ አለብን በቤታችን ተሸሸግን ከረሃብ፣ከስደት ወይንም ከአደጋ ለማምለጥ
ሳይሆን በእግዚአብሔር ታምነን ፊቱን እንድንፈልግ፣
2.በራሳችን ጥበብ ወይም እውቀት ሳይሆን በእርሱ ላይ እምነት ጥለን እንድንኖር ይህ ደግሞ እርሱ ከሚያመጣው ፍርድ ብቻ
ሳይሆን እርሱ ራሱ ከሚያመጣው የዘላለም ሞትም እንድናለን።
3.በፍጹም ልባችን በእግዚአብሔር ላይ ታምነን በምንኖርበት ጊዜ ልናደርግ የምንችለው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር አሁን
ወይም በኃላ ወደ ቤቱ ወደ ገነት በመጥራት ነፃ እስኪያወጣን ድረስ መጠበቅ ብቻ ነው።
4.በወደቀው ዓለም ውስጥ ተቀምጦ እግዚአብሔር አዲስ ዓለም እንዲያመጣ የመጠበቁ ትዕግሥት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት የክርስትና
ባሕርያት አንዱ ነው።
5.የእግዚአብሔር ሥራ እስኪጠናቀቅ በታማኝነት የሚጠባበቁት ከእግዚአብሔር ዘንድ ዘላለማዊ ሽልማትን ይቀበላሉ።
6.እንደ ዓለማዊ ሰዎች ከመኖር ራሳችንን መለየት አለብን። ራሳችን
ከዓለም የምንለየው ክርስቲያን ካልሆኑት ሰዎች በመራቅ አይደለም የእግዚአብሔር ቃል ለዚህ ለወደቀው ዓለም ብርሃንና ጨው እንድንሆን
ያዘናል ይህም ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይመጡ ዘንድ ነው።
'“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጣዕሙን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጪ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም። 'ማቴዎስ 5:13-14' “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ 'ማቴዎስ 5:14
No comments:
Post a Comment