መከራ ሲደርስባችሁ
'ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ 'ያዕቆብ 1:2
መከራ የሚለው ቃል ከሰይጣን ወይም ከዓለም የሚመጣውን ስደትና መከራ ያመለክታል።
1)አማኞች እንደዚህ ያለውን መከራ በደስታ ሊቀበሉት ይገባል።
“ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ፤ ብፁዓን ናችሁ። በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳደዋቸዋልና። 'ማቴዎስ 5:11-12፣'በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤ ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሶአልና። 'ሮሜ 5:3-5 ፣'አሁን በብዙ ዐይነት ፈተና ውስጥ ሆናችሁ ለጥቂት ጊዜ መከራን ብትቀበሉም እንኳ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል።'1 ጴጥሮስ 1:6

2)አንዳንድ ግዜ በአማኞች ሕይወት ላይ መከራ የሚደርሰው እግዚአብሔር የእምነታቸውን እውነተኛነት ለመፈተን ስልሚፈልግ
ነው።በሕይወታችን መክራ መድረሱ ፣እግዚአብሔር በእኛ ላይ የተቆጣ መሆኑን ሁልጊዜ እንደሚያመለክት መጽሐፍ ቅዱስ በየትኛም ቦታ አያስተምርም።ነገር
ግን መከራ በእርሱ ላይ ያለንን ጽኑ እምነት እግዚአብሔር ለማውቁ ምልክት ሊሆን ይችላል።'እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር
ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ። 'ዕብራውያን 10:34፣'ቅጣት
ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል። 'ዕብራውያን
12:11
No comments:
Post a Comment