እምነትና ጸጋ
'በእርሱም በኩል አሁን ወደ
ቆምንበት ጸጋ በእምነት መግባት ችለናል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ተስፋ በማድረግ ሐሤት እናደርጋለን። 'ሮሜ 5:2
ድነታችን ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ ነው፡ይሁን እንጂ ተፈፃሚ የሚሆነው ሰው በእምነት ሲቀበለው ነው፡፡ለድነት የሚያበቃ እምነት፡ እግዚአብሔር ለድነታችን የሚጠብቅብን በክርስቶስ ኢየሱስ እንድናምን ብቻ ነው፡፡በክርስቶስ ማመን ማለት በአፍ የሚገልጽ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን በጌትነቱ ለመከተል ከሚሹ አማኞች የሚመነጭ ልባዊ እርምጃ ነው፡፡
ማቴ 4:19 እርሱም። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ማቴ 16:24 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ። እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ሉቃ 9:23-24 ለሁሉም እንዲህ አላቸው በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል። 25 ሰው ዓለሙን ሁሉ አትርፎ ራሱን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
1)እምነት ማለት የተሰቀለውንና ከሞት የተነሣውን ክርስቶስን እንደግል አዳኛችንና ጌታችን አድርጎ ከልብ ማመንና በእርሱም መደገፍ ማለት ነው ሮሜ 1:17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። በአዲስ ኪዳን ለተገልጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃዳችንንና ሁለተናችንን በማስገዛት በሙሉ ልባችን ማመንን ይኖርብናል፡፡
ሮሜ 6:17-18 ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ። ኤፌሶን 6:6 የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ።ዕብ 10:22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤
2) እምነት በእውነተኛ ጸጸት በክርስቶስ በኩል ከኃጢአት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ማለት ነው፡፡
የሐዋርያት ሥራ 2: 37-38 ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት። ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው። ጴጥሮስም። ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:10 እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።
3) እምነት እግዚአብሔርን በማመን ለእርሱ ምስጋናን በማቅረብ፤በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደትን በማግኘት በሚንሣሣ የኑሮ ዘይቤ ለኢየሱስ ክርስቶስና ለቃሉ መታዘዝን ያካትታል ዮሐንስ 3:3-6 ኢየሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።ኒቆዲሞስም። ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው።ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።ስለዚህ እምነትና መታዘዝ የማይነጣጠሉ ናቸው፡፡ሮሜ 1:5 በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤ሮሜ 16:26 እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፡፡ ራስን ለቅድስና ሳይስጡ ድነት አለኝ ማለት ተገቢ አይደለም፡፡
No comments:
Post a Comment