ለአዲስ ዓመት መመሪያ እንዲሆነን የሚከተሉትን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከታለን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መታደሻ ታሪኮች እና ቃላት ለእያንዳንዳችን ህይወት ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅራዊ እቅድ የበለፀገ ነው ከእነዚህም ።
የእድሳት ተስፋ
'ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፣ አዲስ ሆኖአል። '2 ቆሮንቶስ 5:17
የእግዚአብሔር ጊዜ
'በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር። 'መዝሙር 37:7
ያለፈውን መተው
'“የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ ያለፈውን እርሱ። እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤ 'ኢሳይያስ 43:18-19
ጌታ ለእኛ እቅድ አለው
'ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር ፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም። 'ኤርምያስ 29:11
ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ
'ለነገ ርግጠኛ አለኝታ ይኖርሃል፤ ተስፋህም ከንቱ አይሆንም። 'ምሳሌ 23:18
የልብ እና የመንፈስ መታደስ
'የማያወላውል ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ አዲስ መንፈስ በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ። 'ሕዝቅኤል 11:19
በጌታ እመኑ
'በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል። 'ምሳሌ 3:5-6
Book of Jon
ReplyDeleteWow God bless u.
ReplyDelete