ወንድ ልጅ ትወልዳለች
'ኢየሱስም መልሶ፣ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” አለው። ኒቆዲሞስም፣ “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ እንዲወለድ ተመልሶ ወደ እናቱ ማሕፀንስ ሊገባ ይችላልን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ 'ዮሐንስ 3:3-5
ለእግዚአብሄር ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሄር
ልጅ ለመሆን ብቸኛው መመዘኛ ኢየሱስን መቀበል ነው፡፡'ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። ' ዮሐንስ 1:12
በበረት የተወለደው ኢየሱስ በልባችን
ካልተወለደ አይጠቅመንም፡፡ ሃይማኖተኞች ብዙ መልካም ነገሮችን እንዲሁም አገልግሎቶችን
ለእግዚአብሄር ብለን ልናደርግ እንችላለን፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራው ስራ ለእኔ ነው ብለን
ኢየሱስን እንደግል አዳኛችን አድርገን ካልተቀበልንና ዳግመኛ ካልተወለድን
ኢየሱስ በምድር ላይ መወለድ አይጠቅመንም፡፡ ኢየሱስን ያደንቀው ለነበረ ኒቆዲሞስ ለተባለ የህግ መምህር ኢየሱስ ያለው
ይህንኑ ነው፡፡
በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች
ገናን በፍቅር ልናከብረው እንችላለን፡፡ ኢየሱስን ከልባችን ልናደንቀው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ በልባችን ካልኖረ ወደ ምድር
የመጣበትንና ከድንግል ማርያም የተወለደበትን አላማ ስተነዋል፡፡
'ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።” 'ማቴዎስ 1:21
የኢየሱስ በምድር
ላይ መወለድ ለሰው ልጆች ድህነት ሲሆን ስለተወለደ ብቻ ሰዎች ከመቀፅበት አይድኑም የምስራቹን ቃል
ሰምተው የሚያምኑ ብቻ ናቸው የሚድኑት ስለዚህም ነው ኢየሱስ ለፍጥረት
ሁሉ ወንጌልን ስበኩ ብሎ ያዘዘን ፡፡
'እንዲህም አላቸው፤ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። 'ማርቆስ 16:15-16
የሚድኑት ኢየሱስን እንደ አዳኝ
የተቀበሉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ የምንም ሃይማኖት ተከታዮች ስለሆንን ብቻ አንድንም፡፡ ከሃጢያት የሚያድነን ኢየሱስን እንደ አዳኝና
ጌታ አድርገን መቀበላችን ብቻ ነው፡፡
'“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ '
ዮሐንስ 3:16
ዮሐንስ 3:16
በየእለቱና በየደቂቃው ኢየሱስን
እየተቀበሉና እየዳኑ ነው፡፡ እኛ ግን ኢየሱስን ወደ ልባችን ሳናስባውና በልባችን ሳይወለድ ኢየሱስ በምድር ላይ ስለተወለደ ብቻ
ድነናል ብለን ካሰብን ተታለናል፡፡ የኢየሱስ መወለድ እንዲጠቅመን ወንጌልን ማመን ይጠበቅብናል፡፡ የሚያድነን የእግዚአብሄር ሃይል
የኢየሱስ ስለሃጢያታችን መሞቱን የምስራች ማመን ነው፡፡
'በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው። 'ሮሜ 1:16
No comments:
Post a Comment