የጥበብ መጀመሪያ
‘እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት
መጀመሪያ ነው፤ ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። 'ምሳሌ 1:7
ብዙ ሰዎች ብዙ ጊዜያቸውን እና ሀብታቸውን፣ እውቀትን ለማግኘት ያፈስሳሉ። ልንከተላቸው የምንችላቸው ብዙ የእውቀት አይነቶች አሉ። በአጠቃላይ ግን ዕውቀትን በሁለት መክፈል ይቻላል። የመጀመሪያው ወደ ቀና መረዳትና ወደ በረከት የሚወስደው መልካም ዕውቀት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ አዳምና ሔዋን ከተከለከለው ፍሬ በበሉ ጊዜ ያገኙት ይኸውም በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያስከተለው አይነት ዕውቀት ነው።
የመፅሐፍ ቅዱስ ጠቢብ ተብሎ የሚጠራው ሰለሞን ስለ ቀዳሚው ጥበብ (ዕውቀት) ሲናገር እንዲህ አለ። ”የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” እግዚአብሔርን የማንፈራ ከሆነ የፅድቅ ህይወትን ለመኖር አንሞክር። በልባችን እግዚአብሔርን መፍራት እያለ እንኳን ከስጋችን፣ ከአለምና ከሰይጣን የሚመጡ ፈተናዎች አሉብን።መፅሐፍ ቅዱስ መንገዳችን ሁሉ በእግዚአብሔርና ፊት ግልፅ እንደሆነ ያስታውሰናል። ከእርሱ የተደበቀ አንዳችም የለም። የማይታየው ሀሳብም ሆነ ለእርሱ ምስጢር የሆነ ድርጊት የለም። መገኘቱ በሁሉም ቦታ ነው። ዘማሪው የእግዚአብሔር መገኘት ያልተገደበ እንደሆነና የማይገኝበት ቦታ እንደሌለ አሳምሮ ፅፎልናል። እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ አለ። ይህ እውነት ሲገባን እግዚአብሔርን መፍራት በውስጣችን ያድጋል። በጥበብም እንድንኖር ይረዳናል።
No comments:
Post a Comment