ዓለም
'ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል። '
1 ዮሐንስ 2:17
'እንዲህም አላቸው፤ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ '
ማርቆስ 16:15
ቤተ ክርስቲያን
'እግዚአብሔርም ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም፣ በማንኛውም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾመው። '
ኤፌሶን 1:22
'እርሱ አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረው ዘንድ እርሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኵር ነው። '
ቈላስይስ 1:18
ኀይል
'ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ። '
ፊልጵስዩስ 4:13
'ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው ጒልበት ይጨምራል። '
ኢሳይያስ 40:29
ጥበብ
'ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው፣ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።
'
ያዕቆብ 1:5
' እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል። '
ምሳሌ 2:6

No comments:
Post a Comment