'ሰንበት ካለፈ በኋላ፣ በሳምንቱ
መጀመሪያ ቀን ጎሕ ሲቀድ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ ሄዱ። በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታም
መልአክ ከሰማይ ወርዶ ወደ መቃብሩ በመሄድ ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ላይ ተቀመጠበት፤ ጠባቂዎቹ መልአኩን ከመፍራት የተነሣ ተንቀጠቀጡ፤
እንደ በድንም ሆኑ። መልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር። መልአኩም ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤
የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁና፤ እርሱ በዚህ የለም፤ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል፤ ኑና ተኝቶበት የነበረውን ቦታ
እዩ። አሁንም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ፣ ‘ከሙታን ተነሥቶአል፤ ቀድሞአችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ በዚያ ታዩታላችሁ’ ብላችሁ
ንገሯቸው። እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ!” ሴቶቹም በፍርሀትና በደስታ ተሞልተው ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር በፍጥነት እየሮጡ የመቃብሩን
ስፍራ ትተው ሄዱ። ወዲያው ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሩን ይዘው
ሰገዱለት። ኢየሱስም፣ “አትፍሩ፤ ሂዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሯቸው፤ በዚያ ያዩኛል” አላቸው። 'ማቴዎስ
28:1-10
መቅደላዊት ማሪያምና ሁለተኛይቱ ማርያም የጌታን አካል ሽቶ ለመቀባባት ወደ መቃብሩ ሰንበት ካለፈ በኃላ እጅግ ማልደው መጡ ወደመቃብሩም እየመጡ እርስ በርሳቸውም ድንጋዩን
ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል ይባባሉ ነበር።የጌታ መልአክ ድንጋዪንም አንከባሎ በላዩ ላይ ተቀምጦ ኖሮአል ስለዚህ ወደ መቃብሩ ቀርበው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር
ተመለከቱ።በዚያን ጊዜ መላአኩን አዩ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ስለነበሩ ደነግጡ
መልአኩም ሴቶችን አላቸው
1. “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ?
2. “ተነስቶአል እንጂ በዚህ የለም፥ በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ፣
3. “የሰው ልጅ በኅጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ።”
4. “ጌታ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።
5. “ፈጥናችሁም ሂዱና ከሙታን ተነሳ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።”
በመላዕክቶቹ እንደተነገራት፣ መቅደላዊት ማሪያም መቃብሩ ውስጥ አየች፣ ነገር ግን በአዕምሮዋ ውስጥ የተመዘገበው ነገር የጌታ አካል እንደሌለ ነበር።
ለሐዋርያቶቹ ለመዘገብ ፈጠነች እና ጴጥሮስንና ዮሐንስን አግኝታም እንዲህ አለቻቸው፣ ጌታን ከመቃብር ወስደውታል፣ ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም።ጴጥሮስና ዮሐንስም ወደ ቦታው በመሮጥ፣ “የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ… በራሱ የነበረውን ጨርቅ… ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደነበር።በማየት በትክክል መቃብሩ ባዶ መሆኑን አረጋገጡ። ዮሐንስ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የትንሳኤን አስደናቂ መልዕክት መገንዘብ የቻለው። እርሱ፣ አየም፣ አመነም፣ሲፅፍ ሌሎቹ ግን ለዛ ነጥብ፣ ኢየሱስ ከሙታን ይነሳ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበር።
የኢየሱስ ትንሣኤ የወንጌል እውነቶች ዋንኛው ክፍል አንዱ ነው።'ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምቈጠር ለእኔ ደግሞ ታየ። እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ከዚያም ለኬፋ ታየ፤ ቀጥሎም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንቀላፍተዋል። ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤ በኋላም ለሐዋርያት በሙሉ ታየ፤ '1 ቆሮንቶስ 15:3-8
የክርስቶስ ትንሣኤ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ያለው ጠቀሜታ
1.ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ማረጋገጫ ነው።'መልሼ ለማንሣት ሕይወቴን አሳልፌ ስለምሰጥ አባቴ ይወደኛል። ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ አሳልፌ ለመስጠትም ሆነ ለማንሣት ሥልጣን አለኝ፤ ይህን ትእዛዝ የተቀበልሁትም ከአባቴ ነው።” 'ዮሐንስ 10:17-18
2.የቤዛነት ሞቱ በቂ መሆኑን ያረጋግጣል ።'ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ፣ እኛም እንዲሁ በአዲስ ሕይወት እንድንኖር በጥምቀት ሞተን ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። 'ሮሜ 6:4፣'ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢ አታችሁ አላችሁ ማለት ነው። '1 ቆሮንቶስ 15:17
3.የቅዱሳት መጻሕፍትን እውነተኛነት ያረጋግጣል።'እርሱም፣ “ከእናንተ ጋር በነበርሁበት ጊዜ፣ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል’ ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው” አላቸው። በዚህ ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያስተውሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “ ‘እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ ክርስቶስ መከራን ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፤ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለሕዝቦች ሁሉ ንስሓና የኀጢአት ስርየት በስሙ ይሰበካል፤’ 'ሉቃስ 24:44-47
4.ክፉዎች ወደ ፊት እንደሚይፈረድባቸው ያረጋግጣል።'ቀደም ሲል እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን አለማወቅ በትዕግሥት ዐልፎአል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ ያዛል፤ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ በጽድቅ የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱንም ከሙታን በማስነሣቱ ለሰዎች ሁሉ ይህን አረጋግጦአል።” 'ሐዋርያት ሥራ 17:30-31
5.በየዕለቱ ባለን ተመክሮ የክርስቶስ ህልዎትና ኅይል በኅጢአት ላይ ድል እንዲኖረን ያበቁናል።'ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው። 'ገላትያ 2:20፣'እንዲሁም በእርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ኀይሉን እንድታውቁ እጸልያለሁ። ይህም ኀይል እንደ እርሱ ታላቅ ብርታት አሠራር፣ ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየው ነው። 'ኤፌሶን 1:18-20
ከትንሣኤው በኃላ ክርስቶስ ለሐዋርያትና ለብዙዎች ተከታዮቹ በምታየትና እነርሱንም በማነጋገር አርባ ቀን በምድር ቆይቶአል።
1.ለመግደላዊት መርያም
'መግደላዊት ማርያምም፣ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥታ፣ “ጌታን እኮ አየሁት!” አለች፤ እርሱ ያላትንም ነገረቻቸው። 'ዮሐንስ 20:18
2.ከመቃብሩ ደርሰው ለተመለሱት ሴቶች
'ወዲያው ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት። 'ማቴዎስ 28:9
3.ለጴጥሮስ
'“እነርሱም ጌታ በእርግጥ ተነሥቶአል! ለስምዖንም ታይቶአል” ይባባሉ ነበር። 'ሉቃስ 24:34
4.ለሁለቱ የኤማሁስ መንገደኞች
'በዚሁ ቀን ከደቀ መዛሙርት ሁለቱ፣ ከኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ወደሚርቅ፣ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤ እነርሱም፣ “በመንገድ ሳለን፣ እያነጋገረን ቅዱሳት መጻሕፍትንም ገልጦ ሲያስረዳን፣ ልባችን እንደ እሳት ይቃጠልብን አልነበረምን?” ተባባሉ። በዚህ ጊዜ ዐይናቸው ተከፈተ፤ ዐወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ። አብሮአቸውም በማእድ በተቀመጠ ጊዜ እንጀራውን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ሰጣቸው። 'ሉቃስ
24:13,30-32
5.በክርስቶስና በወንጌሉ የሚያምኑ ሁሉ በውሃ መጠመቅ አለባቸው።ይህም ኢግብረገባዊነትን ዓለምንና የራሳቸው የኅጢአታዊ ተፈጥሮ ለማውገዝና ለመተው የገቡትን ቃል ኪዳን እንዲሁም ለክርስቶስና ለመንግሥቱ ዐላማ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ የሰጡበትን ሁኔታ ይወክላል።'ታዲያ፣ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥተህ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኀጢአትህም ታጠብ።’ 'ሐዋርያት ሥራ 22:16
6.በመንፈስ ቅዱስ ሕልዎትና ኅይል አማካይነት ክርስቶስ ከታማኝ ተከታዮቹ ጋር አብሮ ይሆናል።ለሕዝብ ሁሉ ለመመስከር መሄድ ያለባቸው ከላይ ኅይልን ከለበሱ በኃላ ነው።'እኔም አባቴ የሰጠውን ተስፋ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኀይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቈዩ።” 'ሉቃስ 24:49፣'ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።” 'ሐዋርያት ሥራ 1:8
No comments:
Post a Comment