የዕንባቆም ማጒረምረም
'እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣ አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? “ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣ አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው? 'ዕንባቆም 1:2
አሦራውያን ነነዌ ላይ በተሸነፉበትና ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን በወረሩበት ጊዜ መካከል
(605-597 ዓ.ቅ.ክ) ዕንባቆም ትንቢት ይናገር ነበር።
1)ይህም ለእስራኤል የተነገረ ትንቢት ሳይሆን በነብዩና በእግዚአብሔር መካከል የተደረገ ተዋሣኦ ያለበት ስለ ሆነ ከሌሎች ልዩ ነው።ዕንባቆም ያቀረበው ጥያቄ “እግዚአብሔር በይሁዳ ምድር አይሎ በሚገኘው ክፋት ላይ ለምን አይፈርድም፧’’የሚል ነበር።
እግዚአብሔርም ይሁዳን ይቀጡ ዘንድ ባቢሎናውያንን እንደሚልክ ለቀረበው መልስ ሰጠ።
2)ይህ ምላሽ ነብዩን የባሰ ግራ መጋባት ውስጥ ከተተው፤’’እግዚአብሔር ሕዝቡን በባሰ ኅጢአተኛ ለምን ይቀጣል?ጥያቄም ፈጠረበት።’’በመጨረሻ ግን ዕንባቆም ሁኔታዎች ምንም ይሁኑ ምን እንደ ጌታ ፈቃድ በእግዚአብሔር መታመንና በእምነት መኖርን ተማረ።
No comments:
Post a Comment