የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን
ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።
1) ኢዮብ በደረስበት ከባድ መከራ እጅግ አዝኖ ስሜቱን ገልጾል ፡፡ነገርግን በዚህ የከፋ ሁኔታ እያለ እንኳ ኢዮብ ኅዘኑን የገለጸው በእግዚአብሔር ፈት በፍጹም ትሕትና በመቅረብና እርሱንም ማምለኩን በመቀጠል ነው።
2) ኢዮብ ታማኝ ክርስትያኖች በሕይወት ላይ የሚደርስውን እንዲህ ዐይንቱን ታላቅ መከራ እንዴት መቀበል እንዳለባቸው ያሳያል። በከባድ መከራና ለምን እንደ ደረስብን ልንገልጸው በማንችል ሥቃይ ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ እግዚአብሔር በእኛ ላይ እንዲያልፍ የፈቀደውን ነገር ለመቀበል ትርጉሙን እናውቅ ዘንድ መገለጥንና መረዳትን ለማግኘት እግዚአብሔር ጸጋውን እንዲስጠን መጸለይ ይገባናል ። እግዚአብሔር ጸጋውን እንዲስጠን መጸለይ ይገባናል። እግዚአብሔር ፍቅር እንደመሆኑ በዐመፅ ሳይሆን ፍጹም በእርሱ ላይ በመታመን ግራ የተጋባንበትን ነገርና ቅሬታችንን በፊቱ ይዘን ብንቀርብ እርሱ ለችግራችን መፍትሔ ይስጠናል ።
No comments:
Post a Comment