እውነትም ነጻ ያወጣችኋል!
'እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።” 'ዮሐንስ 8:32
ከሰው ልጆች የዕውቀት ዐውድ
አንጻር ሲታዮ ብዙ ነገሮች እውነት ናቸው፤ሆኖም ሰዎችን ከኅጢአት፣ከጥፋትና ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ሊያወጣ የሚችል አንድ እውነት
ብቻ ነው፤ይህም እውነት በእግዚአብሔር ቃል የሚገኝ የኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው እውነት ነው።ስለ እውነት ልናስተውላቸው ከሚገቡ
ነገሮች አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው።
1)ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም
በክርስቶስና በሐዋርያት የተላለፉት መሠረታዊ መገለጦች ከኅጢአት፣ከዓለምና ከሰይጣን አሠራር ነጻ ስለሚያወጣው እውነት ይመሰክራሉ። 'በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤ 'ኤፌሶን
2:20፤ 'ምክንያቱም የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶስ ኢየሱስ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶአችኋል። 'ሮሜ 8:2፤ 'ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።
'ገላትያ 5:1፣ 'ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም
በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤
ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል። 'ገላትያ 5:1,13
2)የክርስቶስን ወንጌል ፍጹም
ወይም የበለጠ ብቁ ለማድርግ ተጨማሪ መገለጥ አያስፈልግም ፤በራሱ ፍጹም ነውና።
3)ወደ
ድኅነት የሚያደርስ እውነት የሚገለጠው፣”በመንፈሱ”በኩል 'እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም
የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። '1 ቆሮንቶስ 2:10 ከእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ከማንኛውም ሰው ወይም ከሰብአዊ ጥበብ አይመነጭም ።'እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም
የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤
ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማር ነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ
በተማር ነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው። '1 ቆሮንቶስ 2:10,12-13
No comments:
Post a Comment