1. የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንረዳለን:: መዝ 119:105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
2. መንፈሳዊ ጉድለታችንን አውቀን ለማስተካከል እንችላለን! ያዕ 1:22-23 ፤ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ፤ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
3. የተሻለ ሕይወት እንድንኖር ይረዳናል :: ማቴ 4:4 ፤ እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው ኤር 29:11 ፤ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
4. እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማወቅ ይረዳናል:: ሮሜ 10:17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።1 ጴጥ 2:2-3
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን
ወተት ተመኙ።
5. የሕይወት መንገዳችንን ይመራናል:: (ኢያሱ 1:8) የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።
6. መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እግዚአብሔር እንዳንበድል ይረዳናል ።
. መዝ 119:11 አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
7. ከህይወታችን የማያስፈልገውን ይቆርጣል እኛንም ያሳድገናል :: ኤፈ 6:17 ፣
የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
8. ፍሬያማዎች ያደርገናል :: ቆላ 1:11 በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
9. መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እኛ ስለ ወንጌል እንማራለን ፤ ዮሐ 5:39-40 ፤ እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።
10. በእምነት ለማደግ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይጠቅማል:: ሮሜ 10:17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
11. በጥበብ ለማደግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይረዳናል:: መዝ 119:98 ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
12. መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት
ከሁሉ በላይ ኢየሱስን ለማወቅ ይረዳናል ።ማቴ 5:17እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። ሉቃ 24:44 እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ
በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።ዮሐ 5:39እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
13. ከሐሰት ትምህርቶችና ሐሰተኛ ነቢያት ራስህን ለመጠበቅ ይረዳናል :: ማቴ 7:15የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ቆላ 2:8 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
14. ጊዜያችንን በጥበብ ለመጠቀም:: ኤፌ 5:15-16 እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።
Abagolerblan28@yahoo.com
ReplyDeleteReally it is good expression and I got alot from this matrial God bless you
ReplyDelete