ፍቅር ፣ እምነት ፣ ተስፋ እና እውነት!
በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፤በቈላስይስ ለሚኖሩ፣ በክርስቶስ ለሆኑ ቅዱሳንና ታማኝ ወንድሞች፤ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።ምስጋናና ጸሎት ስለ እናንተ በምንጸልይበት ጊዜ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ እናመሰግናለን፤ ምክንያቱም በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለቅዱሳን ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል፤ ይህም የሆነው በሰማይ ተዘጋጅቶ ከተቀመጠላችሁ ተስፋ የተነሣ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ፤ ይህም ወደ እናንተ ደርሶአል። ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው። ይህንም ስለ እኛ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነው፣ አብሮንም በአገልግሎት የተጠመደው ተወዳጁ ኤጳፍራ አስተማራችሁ፤ ደግሞም በመንፈስ ስላላችሁ ፍቅር ነገረን።
ጳውሎስ በደብዳቤ መግቢያ ላይ የጸሓፊውን ስም መጻፍ የተለመደ ነበር ጳውሎስ በመልእክቱ መግቢያ ላይ ስሙን ጠቅሷአል። ጳውሎስ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ሲል ሐዋርያነቱን የተቀበለው በጌታ ጥሪ ስለሆነ ነው። ሐሥ 26:16 አሁንም፣ ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለ እኔ ስላየኸውና ወደ ፊትም ስለማሳይህ ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ተገልጬልሃለሁ።ኤፌ 3:7 እኔም በኀይሉ አሠራር በተሰጠኝ በእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ የዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆኛለሁ።
በቈላስይስ ለሚኖሩ …. ታማኝ ወንድሞች ፤
ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን መልእክት ለቆላስያስ ሰዎች የጻፈው፤ለክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ራስን አሳልፎ መስጠትና የሐዋርያትን አስተምህሮ መከተል ሙሉ ድነትን ለማግኘት የሚያበቃ አይደለም ብለው የሚያስተምሩ የሐሰት ትምህርት አስተማሪያዎች ፣ ቀስ በቀስ ወደ ቤተክርስትያኒቱ ሠርገው እየገቡ ስለነበር ነው። ጳውሎስ በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ሰው እንደነበር ያሳያል።ጳውሎስ የጢሞቲዎስን ስም ሲጠቅስ እዚህ ብቻ ሳይሆን በ2ኛ
ቆሮንቶስ 1:1 በፊልጵስዮስ 1:1 በ1ኛ
እና በ2ኛ ተሰሎንቆ 3:2 እንዲሁም በፊልሞና 1:1 ላይ ጠቅሶታል በመልእክቱ ውስጥ ደጋግሞ እኔ ማለቱ የመልእክቱ ጸሓፊ እርሱ ራሱ እንደነበር ያረጋግጣል።
ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ስላለው መንፈሳዊ አንድነት በቆላስያስ መልእክቱ ላይ 13 ጊዜ ጠቅሶታል ታማኝ ኤፌ 1:3 በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።ቅዱሳን ክርስቶስ በቆላስያስ አማኞች ምትክ ስለ ሞተ የቆላስያስ አማኞች በእግዚአብሔር ፊት ቅዱሳን ናቸው።እንዲሁም ከመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተነሣ ሁልጊዜ በየዕለቱ ኑሮአቸውን ይቀድሳሉ ። ጸጋና ሰላም ዮሐ 14:27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።20:19 በዚያኑ ዕለት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ፣ ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ገላ 1:3 ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ኤፌ 1:2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ከገላትያ መልእክት በስተቀር እያንዳንዱ የጳውሎስ መልእክት እግዚአብሔርን በማመስገን ይጀምራል ፊል 1:3-4 ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።አንተን በጸሎቴ በማስብህ ጊዜ ዘወትር አምላኬን አመሰግናለሁ፤…መጽሐፍ ቅዱስ ሰውን ስል እምነቱና ስላለው ፍቅር አያመሰግነውም፣የእነዚህ መልካም ሥነ ምግባሮች ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን ግን ማመስገን እንደሚገባ ያስተምራል።እናመሰግናለን ይህን ሲል ጳውሎስ ራሱንና ጢሞቲዎስን ማለቱ ነው።በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነት፦ ይህ የቆላስያስ ሰዎች በክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ያለ እምነታቸውን ያሳያል፤ ይህም በወንጌል ሀይል አማካይነት ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለ፦ ይህ እምነት በክርስቶስ ከመሆን የተነሳ የተገኘ መሆኑን ይጠቁመናል። ይህም “በ”
የሚለው ቃል ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነታችንን ይጠቁማል። ለዚህ ማብራሪያ የሚቀጥለውን እንይ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር፦ ይህ ፍቅር ከላይ ከተጠቀሰው እምነት (ይህም የክርስቶስ ከመሆን የተነሳ) የተገኘ ፍቅር ነው። ፍቅር በክርስቶስ ኢየሱስ ከማመን የመነጨ ነው በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሰራ እምነት/ life of faith። ይህም በክርስቶስ መሆንና ለቅዱሳን ሁሉ ያለ ፍቅር ሊለያዩ የማይችሉ አንድ ገጽታዎች እንጂ የተነጣጠሉ መንፈሳዊ ፍሬዎች አይደሉም። ገላ 5:4-6 በሕግ ለመጽደቅ የምትጥሩ፣ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፤ ከጸጋ ርቃችኋል። እኛ ግን ተስፋ የምናደርገውን ጽድቅ፣ በመንፈስ አማካይነት በእምነት ሆነን በናፍቆት እንጠባበቃለን። በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑ፣ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፤ የሚጠቅመውስ በፍቅር የሚገለጽ እምነት ብቻ ነው።ዮሐ 13:34-35“አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብት ዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”
ተስፋ ፣ተስፋ፦ በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተስፋ ነገ ከዛሬ ይሻላል የሚል ግላዊ ጉጉት አይደለም
ተስፋ የተመሰረተው የታመነና ሊዋሽ የማይችለው እ/ር በገባው የተስፋ ቃል ላይ! ከዚህ የተነሳ ተስፋችን ራሱ እግዚአብሔር ነው በብሉይ ያህዌህ የእስራኤል ኪዳናዊ ተስፋ መሰረት እንደነበር መዝ 25:3 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ከቶ አያፍሩም፤ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ። 31:24 እግዚአብሔርን ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ፤በርቱ፤ ልባችሁም ይጽና። 71:5 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።ሰቆቃወ 3:21–ሆኖም ይህን አስባለሁ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ርኅራኄው አያልቅምና።ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ታማኝነትህም ብዙ ነው።ራሴን እንዲህ አልሁት፤ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው።በአዲስ ኪዳን ደግሞ አብ በክርስቶስ ተስፋችን ነው (1 ጢሞ 1:1 በእግዚአብሔር፣ ተስፋችንም በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤ ይህም መዝሙረኞች ያህዌህን እንደ ዓለት የመሰሉት ከዚህ የተነሳ ነው። 2 ቆሮ 1:8-11 ወንድሞች ሆይ፤ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር። በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤ ይህም የሆነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንድንታመን እንጂ፣ በራሳችን እንዳንታመን ነው። እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል።
ይህ ተስፋ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህ ተስፋ ደግሞ በብሉይ ይሰራ የጀመረው በክርስቶስ የፈጸመውና ዳግም ሲመለስ የሚያጠናቅቀው ፕሮጀክት ነው “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ ” ቲቶ 2:11–11 ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛት በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤ ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤ እርሱም ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ሕዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቶአል።ስለዚህ ተስፋ አያሳፍርም።ሮሜ 5:5 ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሶአልና።
በዓለም ዙርያ ከበዓለ ኅምሳ በኃላ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ወንጌል በልዩ ፍጥነት በእያንዳንዱ የሮም ግዛት እንደ ተዳረስ ለማሳየት የተጠቀሰ አባባል ነው ሮሜ 1:8 ከሁሉ አስቀድሜ፣ እምነታችሁ በዓለም ሁሉ በመሰማቱ፣ ስለ ሁላችሁም አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ። 10:18 ገር ግን አልሰሙ ይሆን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በርግጥ ሰምተዋል፤“ድምፃቸው በምድር ሁሉ፣ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ተሰማ።” 16:19 የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
ኤጳፍራ የዚያው አካባቢ ተወላጅ ሲሆን ቆላ 4:12 ምናልባትም የቆላስያስ መሥራች እንዲሁም በአቅራቢያ ያሉት የሎዶቂያና የኢያራ ከተሞች ወንጌላዊ ሳይሆን አይቀርም ።ጳውሎስም ኤጳፍራን ፊሞ 23 ከእኔ ጋር የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆነው ሲል ጠርቶታል።ስለ ቆላስያስ ቤተክርስትያን ችግር የነገረውም ሆነ ይህንን መልእክት እንዲጽፍ ያደፋፈረው ኤጳፍራ ነው ።ኤጳፍራ የሚለውም ስም ፣ኤጳፍሮድተስ ከሚለው ስም በአጭሩ የተወሰደ ሲሆን፣ይህም የተገኘው፣አፍሮዳይት ከምትባለው የግሪክ የፍቅር አምላክ ስም ነው።ኤጳፍራም የጣዖት አምልኮን ትቶ ክርስትያን እንደሆነ ስሙ ያመለክታል።በፊል 2:25 4:18 ላይ የተጠቀሰው አፍሮዲጡ ሁለት የተለያዩ ሰዎች ናቸው።
በመንፈስ ስላላችሁ ፍቅር የክርስትያን ፍቅር ምንጩ መንፈስ ቅዱስ ነው።ሮሜ 5:5 ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሶአልና። የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት።ገላ 5:22
ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት የሚቀበሉ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ አማካይነት አድስ ፍጥረት ነው።{2 ቆሮ 5:17}
ReplyDelete3437
ReplyDelete