Menu
  • HOME
  • ENGLISH
    • Prayer
    • Verses
    • Songs
    • Movie
    • Gallery
    • About
    • About US
  • አማርኛ
    • ጸሎት
    • ቃል
    • መዝሙር
    • ፊልም
    • የፎቶ ማዕከለ
    • ስለ
    • ስለ እኛ
 ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ 'ዘኁልቍ 6:24

'The Lord bless thee, and keep thee: 'Numbers 6:24

እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።”

By  WISDOM No comments:
እውነትም ነጻ ያወጣችኋል!
'እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።” 'ዮሐንስ 8:32
ከሰው ልጆች የዕውቀት ዐውድ አንጻር ሲታዮ ብዙ ነገሮች እውነት ናቸው፤ሆኖም ሰዎችን ከኅጢአት፣ከጥፋትና ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ሊያወጣ የሚችል አንድ እውነት ብቻ ነው፤ይህም እውነት በእግዚአብሔር ቃል የሚገኝ የኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው እውነት ነው።ስለ እውነት ልናስተውላቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው።
1)ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በክርስቶስና በሐዋርያት የተላለፉት መሠረታዊ መገለጦች ከኅጢአት፣ከዓለምና ከሰይጣን አሠራር ነጻ ስለሚያወጣው እውነት ይመሰክራሉ። 'በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤ 'ኤፌሶን 2:20፤ 'ምክንያቱም የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶስ ኢየሱስ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶአችኋል። 'ሮሜ 8:2፤ 'ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። 'ገላትያ 5:1፣ 'ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል። 'ገላትያ 5:1,13
2)የክርስቶስን ወንጌል ፍጹም ወይም የበለጠ ብቁ ለማድርግ ተጨማሪ መገለጥ አያስፈልግም ፤በራሱ ፍጹም ነውና።
3)ወደ ድኅነት የሚያደርስ እውነት የሚገለጠው፣”በመንፈሱ”በኩል 'እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። '1 ቆሮንቶስ 2:10   ከእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ከማንኛውም ሰው ወይም ከሰብአዊ ጥበብ አይመነጭም ።'እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማር ነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ በተማር ነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው። '1 ቆሮንቶስ 2:10,12-13
Newer Post Older Post Home

No comments:

Post a Comment

Popular Posts

  • ወንጌል ምንድነው?
  • የእግዚአብሔር መንግሥት
  • ፍቅር ፣ እምነት ፣ ተስፋ እና እውነት!
  • ብርታት ከእግዚአብሔር ጥበብ
  • የሕይወት መንገድ
  • ታዛዥነት
  • Standing Firm | Full Movie | God’s Sovereignty In Our Struggles
  • እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ
  • የእግዚአብሔር ጥበቃ
  • Acts Of The Apostles

Total Pageviews

Flag Counter

Copyright © 2016 STRENGTH IN WISDOM